Top Ad unit 728 × 90

Trending

random
.

Response to Commission of Inquiry on Human Rights in Eritrea Report

To
Commission of Inquiry on 
Human Rights in Eritrea

AMHARIC VERSION 

Kibra Abraham Jurnalist/Author/Producer

1/9/2016



Kibra Abraham Kibraabraham@gmail.com 10 West Run Road Morgantown, WV 26508 (703)-860-8036

 ቅጣት ከተባለስ መጀመሪያ ያጠፋው ይቀጣ

ወደ ተስፋይቱ ምድር አሜሪካ ከገባሁ አስርት ዓመታት ቢያልፉም መጀመሪያ የገባሁበትን ቀን አልዘነጋውም፡፡ ክፉው ዘመን ለረጅም ጊዜያት ከለያየን ቤተሰቦቼ ጋር የተገናኘሁባት የጆንኤፍ ኬኔዲ አየር ማረፊያ ባለውለታዬ ናት፡፡ እንደ ሰንሰለት የተያያዙትን ፎቆች እያሳበርንና የተንጣለለውን ጎዳና እየጎረድፈን ብንከንፍም ኒው ዮርክ በምትሃት  እንጂ በሰው ኃይል የተሰራ አልመስል አለኝ፡፡ መደነቅም ታስደንቀኝ ዘንድ እቤት ስንደርስ በእናቴ እልልታ የደመቀው አቀባበል የዶሮ ወጡ፡ እጣንና የቡና ሽታ አየሩን አውዶት በትዝታ ሰመመን ወደ አገሬ ወሰደኝ፡፡ በባህል እቃ ያበደው እንግዳ መቀበያ መኾንቢያ፣በርጩማው፣መሶቡ ትንሽ ሙዚዬም አስመስለውታል፡፡የዓለም ዋና ከተማ ትልቋ ፖም ውስጥ ቤቴን፣ቤተሰቤን፣እናቴንና አገሬን አገኘኋቸው! ንሳ ማነህ እስቲ ጎድ ብሌስ አሜሪካ በልልኝ!!! አሁን አንድ ወንድሜ፣ እህቴና ከአስመራ ለትምህርት በልጅነቱ የመጣው የአክስቴ ልጅ ቀርተዋል፡፡ እነሱንም አንድ ቀን አገኛቸዋለሁ ብዬ ተስፋ አደረኩ ሁለተኛ የማላገኘው አባቴንም እያስታወስኩና በቅሬታ እየተሞላሁ...!

አባቴ በሃምሳዎቹ ነበር ከትውልድ አገሩ ተነስቶ አዲስ አበባ የገባው፡፡ምንም እንኳ የጣልያኖች አዳሪ ትምህርት ቤት ቢያድግም የባህሉ ተጽእኖ ከኮነሊያል አስተዳደሩ እጅግ ከፍተኛ ስለሆነ ቤተሰብ የመረጠለትን ውብ ኮረዳ መዳር ነበረበት፡፡ ኑሮውንም ሁለት ቦታ አድርጎ የቅርብ ዘመዱ የሆኑት ራስ ተሰማ ቤት እየደወለ የቤተሰቡን ደህንነት ይከታተላል፡፡ እንደ አጋጣሚ ሆኖ ግን እኔ ስወለድ ቤተሰቡ አንድ ላይ ተጠቃለለና በባህላችን መሰረት ሴት ስትወለድ እልል የሚባለው ሶስት ጊዜ ብቻ ቢሆንም ለሴቶቹ ግርምት እንደ ወንድ ሰባት ጊዜ አልሉላት ብሎ በእጁ ተቀበለኝ፡፡ ለእሱ ብቻ ከሚሰራው ፓስታ የማባላው ብቸኛ ተሳታፊም ሆንኩ፡፡ እኔም ብሆን በትግርኛና ጣልያንኛ መሃል የሚወላገደውን አማርኛውን አስተካክልለት ነበር፡፡ ግኑኝነታችን በመከባበር የተመሰረተ ነበርና ፀሃይ ስትጠልቅ የሚከተለውን ነፋሻ አየር ለመቀበል አስቂኝ ገጠመኞችን እያወራን የእግር ጉዞ የምናደርግበት ጣፋጭ ጊዜም ነበረን፡፡

ታዲያ አንዱን የመስከረም ተሲያት የተለመደውን የእግር ጉዞ ለማድረግ ከሁለት እህቶቼ ጋር ትንሽ እንደሄድን በአስደንጋጭ ድምጽ አባቴ ከመሃላችን ወደቀ፡፡እኔ ትንሽዋ እህቴን ሳቅፍ ታላቅ እህቴ የመታውን ሰው አባራ ለመያዝ የሞት ሞቷን አሯሩጣው አልሆንልሽ ቢላት ጭቃ ውስጥ የቀረውን አንዱን የእግር ጫማ ለማስረጃ ይዛ ተመለሰች፡፡ ደሙ ለሚጎርፈውም አባቴ ትራስ ሆና እኔን ሰው እንድጠራ ቤት ላከችን፡፡ እኔም የሆነው ሁሉ ህልም ቢመስለኝም- እንባዋ ደርቆባት ልብሷ በደም የተበከለው እህቴ በእንባ የታጠበችውን ትንሽዋን አዝላ ስትመለስ ሰው እንደጎደለኝ ታወቀኝ፡፡ ከዚያማ ኤርትራኖች በማይታወቅ ሰው እየተገደሉ መገኘት ደንብ ሆኖ ቀረ፡፡

ደርግ ሲተካም ተቀጥያ ስም ወጥቶላቸው በግልጽ የሚታደኑበት ሁኔታ ተፈጠረና አጎቶቼ፣ዘመዶቼ፣ወንዱም፣ሴቱም ታድኖ ከመሞት አንድኛውን ጫካ ገብተው ይለይለት አሉ...! የኢ.ህ.አ.ፓ. አባላት ሆነው ከፍተኛውን ቁጥር ይዘው የተገደሉት፤ ለኢትዮጵያ ልዩ ኃይል ሆነው ከወንድሞቻቸው የተዋጉ፤ በአስመራ ጎዳናዎች በየመንገዱ በሽቦ የታነቁት፤ በየእስር ቤቱ የተረሸኑት፤ የእንግሊዝና የአፄው ሃይማኖተኞች ጎራ ለይተው የተላለቀት በሙሉ ዛሬ ልጆቻቸው እንደ እህል ዘር ለመበተናቸው ትልቅ አስተዋፅኦ አድርጓል፡፡ እኔም ዛሬ እዚህ እውነት ላይ ቆሜ ነው “Systematic, Widespread and gross human rights violations.” የሚል ፅሑፍ አይቼ ብእሬን የመዘዝኩት፡፡ እኔ አንዲት ተራ ስደተኛ ሴት ነኝ እኔነቴን፣ባህሌን፣ህዝቤንና አገሬን ጠንቅቄ አቃለሁ፡፡ እንኳን ለሰው ለእንሰሳ ትልቅ ክብር ያላት አሜሪካ ውስጥ የሚኖሩ ብሩህ ዜጎች ግን የአንዲትን አገር ህዝብ ለአገራቸው ያላቸውን የልኡላዊነት ጥልቅ ክብርና ባህላችንን ካለመረዳት የተነሳ የሚያዋርድ ብሂሎችን ማየቴ በጣም አዝኛለሁ፡፡ ለብዙ ዘመናት ሰቆቃና ግድያ ስለተፈራረቁበት የኤርትራ ሕዝብና ወደር ባጣለት ግፍ በድብቅና በተዘዋዋሪ ስለተገፋችው ኤርትራ ነው ዛሬ ሙሾ ይረገድ የተባለው!“Systemic...” ከተባለስ ኤርትራ ትበለው! ጥፋት ያጠፋ ይቀጣ ከተባለ መጀመሪያ ያጠፉት እንግሊዞች ይቀጡ! መቼም ዛሬ ዝርዝር ውስጥ እናዳልገባ ታቃላችሁና በ1952 አቶ ጆን ፎስተር ዳላስ ያሉትን ላስታውሳችሁና እኔ ወደማቀው ጉዳይ አልፋለሁ በጥሞና ተመልክታችሁም ማስተካከያ ታበጁ ዘንድ እማጸናለሁ፡፡

-------
Continue reading:




Sponsored Ads
Response to Commission of Inquiry on Human Rights in Eritrea Report Reviewed by Admin on 12:02 AM Rating: 5

No comments:

All Rights Reserved by Madote © 2016

Contact Form

Name

Email *

Message *

Powered by Blogger.